በመሰራት ላይ ያለው ቤተ ክርስቲያን

የቂርቆስ አምባ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የቤተክርስቲያኒቷን ታሪክ ለማስተዋወቅ እንዲሁም በጅምር ያለውን ግንባታ የሚያግዝ ገቢን ለማሰባሰብ በማሰብ ይህ ድረገጽ ተሰርቶ ተለቅቋል። ድረገጹ ኢ.ኤ.ኤስ. ሶፍትዌር ቴክኖሎጂስ በተባለ ድርጅት ያለምንም ክፍያ የተሰራ መሆኑ ታውቋል።

ቤተክርስቲያኑ የሚገኝበት ተራራ

የቂርቆስ አምባ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የቤተክርስቲያኒቷን ታሪክ ለማስተዋወቅ እንዲሁም በጅምር ያለውን ግንባታ የሚያግዝ ገቢን ለማሰባሰብ በማሰብ ይህ ድረገጽ ተሰርቶ ተለቅቋል። ድረገጹ ኢ.ኤ.ኤስ. ሶፍትዌር ቴክኖሎጂስ በተባለ ድርጅት ያለምንም ክፍያ የተሰራ መሆኑ ታውቋል።

የምዕመናን ጉዞ

የቂርቆስ አምባ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የቤተክርስቲያኒቷን ታሪክ ለማስተዋወቅ እንዲሁም በጅምር ያለውን ግንባታ የሚያግዝ ገቢን ለማሰባሰብ በማሰብ ይህ ድረገጽ ተሰርቶ ተለቅቋል። ድረገጹ ኢ.ኤ.ኤስ. ሶፍትዌር ቴክኖሎጂስ በተባለ ድርጅት ያለምንም ክፍያ የተሰራ መሆኑ ታውቋል።

http://arsema.eotc.org.et/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/244301arsema.jpg http://arsema.eotc.org.et/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/710205mountain.jpg http://arsema.eotc.org.et/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/406245pilgrimage.jpg
የገዳሙ አበምኔት መልዕክት
ለድምጹ ጥራት ይቅርታ እንጠይቃለን

እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር እራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ /ማቲ 16÷24/

ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚያስተምርበት ሰዓት ይህን ቃል ለተሰበሰቡት አስተላልፏል፡፡ ሰው ከሁሉም የሚከብደው እራሱን መካድ ነውና፡፡ ምክንያቱም በሚያየው አለም የማያየውን አለም መለወጥ ከባድ ነው፡፡

ቅድስት አርሴማ ግን አባቷን እናቷን ቤተሰቦቿን ትታ ወደገዳም ስትገባ አልከበዳትም በገዳሙ ስትኖር ብዙ ፈተናዎችን ታግሳ እንዳለች በዲዎቅልጥያኖስ ላይ ሰይጣን አድሮ በሀገሬ ግዛት ውስጥ መልከመልካም ሴት ፈልጋችሁ አምጡልኝ በአካል ማምጣት ባትችሉ ሰዕሏን ስላችሁ አምጡልኝ አላቸው፡፡ እነሱም ሀገር ለሀገር ቢንከራተቱ ለንጉሱ ደስ የምታሰኝ ሴት አላገኙም ወደገዳም ስገቡ ግን ቅድስት አርሴማን አይተው ደስ አላቸው፡፡

ሰአሊዎቹም ቅድስት አርሴማን ስለው አመጡለት ደስ ብሎአቸው የቅድስት አርሴማ ስዕልም ለንጉሱ ወስደው ሰጡት ንጉሱም ደስ አለው በመልኳና በውበቷ ተማረከ ቅድስት አርሴማም ንጉሡ እንደሚፈልጋት ስለሰማች ደነገጠች የንጉሱን ግዛት ለቃ ወደ አርማንያ ሀገር ተሰደደች የተሰደደችበት ሀገር ንጉሡ ድርጣድስ እሷን ይዞ እንዲጠብቀው መልክት ላከበት ድርጣድስም እሷን ባየ ጊዜ ለራሱ ፈለጋት ሁለቱም ንጉሶች በዘመናቸው በክርስቲያኖች ላይ ብዙ መከራና ስቃይ ያደርሱባቸው ነበር። ንጉስ ድርጣድም ቅድስት አርሴማን ይዞ ንግስት አደርግሻለሁ አላት እሷም አንተ ጣዎት አምላኪ በክርስቲያኖች ላይ ግፍ የምታደርስ አንተን አልፈልግም እኔ የምፈልገው አምላኬን ኢየሱስ ክርስቱስን ነው እያለች ክርስቲያኖችን በማበረታታትና አይዞአችሁ አትፍሩ የዚህ አለም መከራ ያልፋል እያለች ክርስቲያችን በማጽናናት መስከረም 29 ቀን ተሰይፋለች። የሰማይትነትንም አክሊል ተቀብላለች።

እኛም ከቅድስት አርሴማ የምንማረው ምንም እንኳን መከራ ቢበዛ ባለንበት ቦታ እግዚአብሔርን እንድናገለግል መሆን አለበት። በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ብንኖር ሁሉም ሀገር የእግዚአብሔር ስለሆነ እግዚአብሔርን ማመስገን ይገባናል፡፡ አስራቱን በኩራቱን እንድንሰጥም እግዚአብሔር ይፍቀድልን ሁሉንም ባለንበት ይጠብቅልን፡፡

ወስሐት ለእግዚአብሔር!

እርዳታ ይለግሱ

በእግዚአሔር ቅዱስ ፈቃድ ለተጀመረውን የቤተክርስቲያን ግንባታ እገዛ በማድረግ የበረከቱ ተሳታፊ ይሁኑ!

እርዳታ ይለግሱ
 
የአሸተን ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ድረ ገጽ ተለቀቀ

eas-profileየቂርቆስ አምባ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የቤተክርስቲያኒቷን ታሪክ ለማስተዋወቅ እንዲሁም በጅምር ያለውን ግንባታ የሚያግዝ ገቢን ለማሰባሰብ በማሰብ ይህ ድረገጽ ተሰርቶ ተለቅቋል።

ድረገጹ ኢ.ኤ.ኤስ. ሶፍትዌር ቴክኖሎጂስ በተባለ ድርጅት ያለምንም ክፍያ የተሰራ መሆኑ ታውቋል። የድርጅቱ ስራ አስኪያጅም ይህንን ስራ በመስራት ከቅድስት እናታችን በረከት ለመካፈል በመቻላቸው እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ሌላውም የበኩሉን እርዳታ በማድረግ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አስተላልፈዋል።

እርዳታ ይለግሱ

በእግዚአሔር ቅዱስ ፈቃድ ለተጀመረውን የቤተክርስቲያን ግንባታ እገዛ በማድረግ የበረከቱ ተሳታፊ ይሁኑ!

ግጻዌ

አድራሻ

በሰሜን ወሎ ሐገረ ስብከት
አሸተን ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን
ቀበሌ 03
ላሊበላ ከተማ

ኢ-ሜይል፡ info@arsema.eotc.org

ቴሌፎን: +251 911 0087796